Faith – ሃይማኖት

Download PDF

ሃይማኖት ፤ ሃይመነ አሳመነ ፤ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም በአንድ አምላክ ማመን እና ለአንድ አምላክ መታመን ማለትን ያመለክታል ፤ በዓይናችን ለምናየው ለግዙፉ ዓለምና ለማይታየው ለረቂቁ ዓለም ፈጠሪ አስገኝ ፣ መጋቢ አለው ፤ እሱም እግዚአብሔር ነው ብሎ ማመን የሃይማኖት የመጀመሪያ ክፍል ነው ።

እምነት ማለትም ፤ አምነ አመነ ፣ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሆኖ ትርጉሙም ለእግዚአብሔር መታመንንና በእግዚአብሔር ማመንን ይገልጣል። ቅዱስ ዻውሎስ “ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደተፈጠሩ የሚታየውም ከማይታየው እንደሆነ እናውቃለን” ዕብ 11 ፥ 3 ። በማለት እንደተናገረ ። የሰው ልጅ የሃይማኖት ትምሕርት ከመማሩ አስቀድሞ በህሊናው በመመራት የእግዚአብሔርን መኖር ማመን ተገቢ ነው ።

የሃይማኖት ትምሕርት ፤ የሚነገረው የእግዚአብሔር ቃል እውነት መሆኑን በመቀበል የምናምነው ን የምንማርበት እንጅ ፣ እንደ ዓለማዊ የሳይንስ ዕውቀት የተማርነው ን ሁሉ በዘመናዊ መሳሪያ አረጋግጠን የምንደርስበት አይደለም ። ሃይማኖት ቁስ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት ታምነቀው ኢየሚኖሩት ሕይወት ነውና ። የእግዚአብሔር መንግሥት ተቃዋሚዎች አጋንንት ሳይቀሩ አይጠቀሙበትም እንጅ የአምላክን መኖር ያምናሉ ይንቀጠቀጣሉም ። ያዕ 2 ፥19 ።

በዚህ ዓለም በራሱ የተገኘ ምንምነገር እንደሌለና ለሁሉም አስገኝ ፤ ፈጣሪ እንዳለው ይታወቃል ። የሳይንሱ የምርምር ውጤ ት፡ ሁሉን የፈጠረው ን ኃይል በሥጋዊ ጥበብ ተመራምሮ አልደረሰበትም ። በሃይማኖት ትምሕርት ግን ሁሉን ያስገኘ እግዚአብሔ ር መሆኑን መረዳት ይቻላል ። የሰው ልጅ የሠራቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሚያንቀሳቅስ ባለሞያ እንደሚያስፈልጋቸው ሁሉ ይህን ዓለምም የሚያንቀሳቅሰውና የሚመራው ፤ አስገኝው (የፈጠረው) አምላክ ብቻ ነውና ። ሰው ይህን የአምላክ ሥራ አይቶ ፈጣሪውን ማመስገን ሲገባው “የተፈጥሮ ክስተት ነው” ሲል ይደመጣል ።

ለምሳሌ ጨለማና ብርሃንን ፣ ወቅቶችንና ዘመናትን ፣ የሚያፈራርቅ ፣ የሰውን ልደትና ሞት የሚወስን ፤ ሌሎችም ፍጥረታት ሥርዓታቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ የሚያደርግ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠራቸው አምላክ ብቻ ነው ፤ የሰው ልጅ የተደረጉና ያለፉ ታሪኮችን ከመመዝገብ ያለፈ ችሎታና አቅም የለውም ።

እምነት ፤ ቅዱስ ዻውሎስ “በሥጋ ዓይን የማናየውንና ተስፋ የምናደርገውን የሚያስረዳና የሚያስረግጥ መሳሪያ ነው ። ዕብ 11 ፥ 1 ።” በማለት እንዳስተማረ ፤ በሃይማኖት የሚኖር ሰው ዕለት ዕለት በሚ ያደርግለት የቸርነት ሥራው አምላኩን ያየዋል ለማ ያምንና ፍረጥረታዊ ለሆነ ሰው ግን የሃይማኖት ነገር ለእሱ ሞኝነት ስለሆነ ለህሊናው ሊረዳውና ፡ሊቀበለው ኤይችልም ። 1ቆሮ 2 ፥ 9 ።

ሃይማኖት ፤ ሰዎችና እግዚአብሔር የሚገናኙባት መንታነት የሌለባት አንዲት መንገድ ናት ። ኤፌ 4 ፥ 4 ። በዓለማችን የሚገኙት የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት የግል ጥቅምና የሥልጣን ሱስ የተጠናወታቸው ፣ ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ ለራሳቸው ክብርና ዝና ቅድሚያ የሚሰጡ ፤ አዲስ ነገር በመሥራት ታዋቂነትን ለማትረፍ የሚፈልጉ ግለሰቦች የመሠረቷቸው ድርጅቶች መሆናቸው ግልጽ ነው ። ምክንያቱም ፤ ሁሉም እየተለዩ የወጡት ከመጀመሪያዋ አንዲት ሃይማኖት ነውና ፤

ሃይማኖት ከቅዱሳን መላእክት ጀምሮ ፀንቶ የሚኖር የአምላክና የፍጡራን ግንኙነት ነው

  • ለምሳሌ ቅዱሳን መላእክት ፤ ሰይጣን ፡ዲያብሎስ “ፈጣሪ ነኝ” ባለበት ወቅት ቅዱስ ገብርኤል “አምላካችን እስኪገለጥልን ድረስ በእምነ ታችን እንጽና” ብሎ የተናገረውን ቃል ፤ መሪ በማድረግ በሃይማኖት ጸንተው ተገኝተዋል ። ራዮሐ 12 ፡7 ።
  • ከአዳም እስከ ሙሴ ፤ የነበሩ ቅዱሳን ሰዎች ፤ የተጻፈ ህግ ሳይኖራቸው በህገ ልቡና እየተመሩ በሃይማኖት ጸንተው ኖረዋል ።
  • ከሙሴ እስከ ክርስቶስ ፤ የነበሩ ቅዱሳን ሰዎች ፤ ቃሉን ሰምተው በመጠበቅ በሃይማኖታቸው ተመስክሮላቸው አልፈዋል ።
  • ሐዋርያት ፤ ቃሉን ሰምተው ፣ ተአምራቱን አይተው ፣ ሀብተ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ሃይማኖታቸውን ጠብቀው ፣ ለሌላውም አስተምረው ክርስትናን በዓለም አስፋፍተው በክብር አልፈዋል ።
  • ከሐዋርያት በኋላ የተነሱና እስከ ዓለም ፍጻሜ የሚቀጥሉ ክርስቲያኖች ፤ ከቅዱሳን ሕይወትና ከመጻህፍት ተረድተው ፣ ከመም ህራን እየተማሩ ፣ በየዘመናቱ የሚደረገውን ተአምራት እያዩ ፤ በሃይማኖት ጸንተው ኖረዋል ፣ ይኖራሉም ። ስለዚህም ሃይማኖት በአምላክ ፈቃድ የሆነና በዘመናት ሁሉ የነበረ ያለና የሚኖር ሕይወት ነው ።

ሃይማኖት ፤ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ሆነው ምሥጋና በማቅረብ ክብሩን ወርሰው እንዲኖሩ የሚያችል ሕይወት ነው
ከዚህ ከተቀደሰና ከትትክለኛው መንገድ የወጡ ሰዎች ከመጠራጠር ተነስተው እኛ ትንንሽ ከርስቶሶች ነን እስከ ማለት ደርሰ ዋል ። ሰው ለህሊናው ገደብ ካላበጀለትና ለእግዚአብሔር ክብር መስጠትን ከረሳ መጨረሻው ጥፋት መሆኑን እንረዳለን ።

5 ሃይማኖት ፤ በዘመናት ብዛት የማታረጅ ፣ የማትታደስ ፣ በየዘመኑ በሚነሳ ሥልጣኔ የማትለወጥ ሁሌም አዲስ ናት ። ሃይማ ኖት ፤ በልብ አምኖ በአንደበት መስክሮ የሚዳንበት ህይወት ነው ። ሮሜ 10 ፥ 10 ። ሃይማኖታችን በምግባር የሚገለጥ መሆን አለበት ። በሥራ የማይገለጥ ሃይማኖት ነፍስ የተለየችው ሥጋ “በድን” ማለት ነውና ። ያዕ 2 ፥ 26 ።