Close
  • Home
  • News & Events
    • Church News | ዜና
    • Events | ዝግጅቶች
    • Calendar | የቀን መቁጠሪያ
  • Services
    • Become a Member
      አባል ይሁኑ
    • Event Space Rental
      የዝግጅት ቦታ ኪራይ
    • Sunday School
      የሰንበት ት/ቤት
    • Sacraments
      ቅዱሳን አገልግሎቶች
    • Kids Service
      የልጆች አገልግሎት
    • Youth Services
      የወጣቶች አገልግሎት
    • Liturgy & Sermons
      ቅዳሴ እና ስብከት
    • Forms Hub | ቅጾች
  • Resources
    • Spritual Books
      መንፈሳዊ መጽሓፍት
    • Geʽez Lesson
      የግእዝ ትምህርት
    • Helpful Links
      ጠቃሚ ምንጮች
    • Galleries | የፎቶ ማህደር
    • Mezmurs | መዝሙራት
  • About
    • About Us | ስለ እኛ
    • Contact | ያግኙን
  • Church Store
  • Account
  • Donate
  • Home
  • News & Events
    • Church News | ዜና
    • Events | ዝግጅቶች
    • Calendar | የቀን መቁጠሪያ
  • Services
    • Become a Member
      አባል ይሁኑ
    • Event Space Rental
      የዝግጅት ቦታ ኪራይ
    • Sunday School
      የሰንበት ት/ቤት
    • Sacraments
      ቅዱሳን አገልግሎቶች
    • Kids Service
      የልጆች አገልግሎት
    • Youth Services
      የወጣቶች አገልግሎት
    • Liturgy & Sermons
      ቅዳሴ እና ስብከት
    • Forms Hub | ቅጾች
  • Resources
    • Spritual Books
      መንፈሳዊ መጽሓፍት
    • Geʽez Lesson
      የግእዝ ትምህርት
    • Helpful Links
      ጠቃሚ ምንጮች
    • Galleries | የፎቶ ማህደር
    • Mezmurs | መዝሙራት
  • About
    • About Us | ስለ እኛ
    • Contact | ያግኙን
  • Church Store
  • Account
  • Donate
0
የቀለበት ቡራኬ <br> Ring Blessing

የቀለበት ቡራኬ
Ring Blessing

Category: የጋብቻ ፕሮግራም Tags: ring, wedding
  • Description

Description

የቀለበት ቡራኬ

የጋብቻ ሕይወት፣ የሰው ልጅ ፈቃደ ሥጋዉን እንዲፈጽምበት፣ ዘሩን እንዲተካበትና እንዲረዳዳበት እግዚአብሔር አምላካችን ያዘጋጀው ሥርዓት ነው፡፡ በስእለት ወይም በሌላ ምክንያት ለመመንኰስ ከወሰኑ አባቶችና እናቶች በቀር ለሰብአዊ ፍጡር ዂሉ ጋብቻ አስፈላጊ ነው፡፡ ስለዚህ ወይ በጋብቻ አለዚያም በድንግልና መጽናት እንጂ እንዲሁ እየዘሞቱ መኖር ኀጢአት ነው፡፡ ትዳር ለመመሥረት ወስነን ዝግጅት ላይ የምንገኝ ምእመናንም የጋብቻ መሥፈርታችን ሃይማኖትን፣ ክርስቲያናዊ ምግባርንና መልካም ሰብእናን መሠረት ያደረገ ሊኾን ይገባዋል፡፡ ሀብትን፣ ዝናንና ውበትን ምክንያት አድርጎ መተጫጨት መጨረሻው አያምርምና፡፡ እነዚህ ቁሳውያን መሥፈርቶች ከጊዜ በኋላ ሲጠፉ ጋብቻም አብሮ ሊፈርስ ይችላል፡፡ ስለዚህም መሥፈርታችን ከሃይማኖትና ከምግባር ጋር የተገናኘ መኾን ይኖርበታል፡፡ እነዚህ ከተሟሉ ሀብቱና ሌላው ጉዳይ በጊዜ ሒደትና በጥረት የሚመጣ ነውና፡፡

ጋብቻ፣ የመለኮትና የትስብእት ምሳሌ ነው፡፡ ‹‹እፎ ቤተ ነዳይ ኀደረ ከመ ምስኪን፤ እንደ ምስኪን እንዴት ከደሃ ቤት አደረ?›› እንደ ተባለው እግዚአብሔር አምላካችን ለተዋሕዶ የመረጠው የድሆችን ሥጋ ነው፡፡ የተዋሕዶ ምሳሌ የኾነዉን ጋብቻ የምንመሠርት ምእመናንም ሰዎችን ገንዘብ፣ መልክ፣ ዝና የላቸውም ብለን ልንንቃቸውና ከምርጫ ውጪ ልናደርጋቸው አይገባም፡፡ ጋብቻ፣ አንደኛው የሌላኛውን ድክመት እየሸፈነ የሚኖርበት እንጂ በሁለት ፍጹማን ሰዎች የሚመሠረት ሕይወት አይደለም፡፡ ፍጹም አመለካከት ያለዉን ሰው ማግኘት ይከብዳልና፡፡ በመኾኑም ጥንካሬያችንን በመጋራት፣ ድክመታችንን በማስተካከልና በመተራረም ለመኖር መዘጋጀት ይኖርብናል፡፡

ጠቢቡ ሰሎሞን “እንደ ቀለበት በልብህ አኑረኝ”  በማለት እንደ ተናገረው (መኃ. ፰፥፮)፣ ጋብቻ ለሚጠብቁትና ለሚያከብሩት ሰማያዊ ዋጋ የሚያስገኝ የፍቅርና የአንድነት ሕይወት ነው፡፡ ለቃል ኪዳን የሚታሰረው ክብ ቀለበትም የጋብቻ ሕይወት የማይቋረጥ አንድነት መኾኑን የሚያመላክት ምሥጢር አለው፡፡ በመተጫጨትና በቃል ኪዳን ቀለበት የተመሠረተው ጋብቻ በሥርዓተ ተክሊል ይፈጸማል፡፡

በዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው

Related products

  • የተክሊል ጋብቻ <br>Holy Wedding

    የተክሊል ጋብቻ
    Holy Wedding

    Read more


St. Teklehaimanot Orthodox Tewahedo Church Ottawa | +1 613-722-6702
Designed and Developed by Yonatan Amare | +251-961445000
© Copyright 2024 All Rights Reserved.

✕