Description
ፀሎተ ፍትኅት
ፍትሐት ማለት ከኃጢአት እስራት መፍታት ወይም መፈታት ማለት ነው፡፡ ስለዚህም ለሞቱ ሰዎች የሚደረገው ጸሎት ጸሎተ ፍትሐት ይባላል።
ጸሎተ ፍትሐት ለበደሉት ሥርየት ኃጢአትን፣ ይቅርታን ዕረፍተ ነፍስን ያሰጣል፡፡ ለደጋጎች ደግሞ ክብርን፣ ተድላን፣ ዕረፍትን ያስገኛል፡፡
ሙታን ጸሎተ ፍትሐት እንዲደረግ፣ መሥዋዕት እንዲቀርብላቸው በቤተ ክርስቲያንና በመካነ መቃብራቸው እንዲጸለይላቸው ቅዱሳን ሐዋርያት በቀኖና ሐዋርያት አዝዘዋል፡፡ በክርስቶስ አምነው ስለሞቱ ወንድሞቻችሁ ክርስቲያኖችና ሰማዕታት በቤተ ክርስቲያን ያለሐኬት ተሰብሰቡ፡፡ በቤተ ክርስቲያን መሥዋዕት ሠውላቸው፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን ወደ መቃብር ስትወስዱአቸውም መዝሙረ ዳዊት ድገሙላቸው፡፡ ዲድስቅልያ አንቀጽ 33 ገጽ 481
ጸሎተ ፍትሐት የዘሐን ጊዜ ጸሎት ነው፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ በእናንተ ባለው መሠረት ከመንጋው መካከል በሞተ ሥጋ የተለዩትን ምእመናን በጸሎትና በዝማሬ እንሸኛቸዋለን፡፡ /ያዕ. 5፤13/ ጸሎተ ፍትሐት የሚደረገው ለከሀድያንና ለመናፍቃን ሳይሆን ለሃይማኖት ሰዎች ነው፡