Description
የተክሊል ጋብቻ
ተክሊል ማለት ክብር ማለት ሲሆን ቃሉም ከለለ አከበረ ጋረደ ከሚለው ግስ የወጣ ዘር ነው።በተክሊል ወንድ «የባሏ ክብር ናት»የተባለች ረዳቱን በፅኑ ኪዳን ወይም በመንፈስ ውል የሚቀበልበት ስለሆነ የተክሊል ጋብቻ የከበረ ነው።ለሴቷም እንዲሁ።እንዲሁም በእግዚአብሄር ስለሚቀደስና ስለሚከበር የተክሊል ጋብቻ
ቅዱስ ነው። ዕብ1÷12
የመጀመሪያው ጋብቻ በእግዚአብሄር ፈቃድ በኤደን ገነት እንደተመሰረተ ሁሉ ዛሬም ስርአተ ተክሊል በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይፈፀማል።
ዘፍ1÷22 በመሆኑም ስርአተ ተክሊሉ የተሞላ የሚሆነው ፀሎት ተክሊሉ ተፈፅሞ ወጣቶች ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበሉ ብቻ ነው። ለዚህ ክብርና የተቀደሰ ጋብቻ ለመብቃትም የሚያስፈልጉ ነገሮች።
1.የሀይማኖት አንድነት
ወጣቶች በሀይማኖት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች መሆን አለባቸው።
2.ድንግልና
የተክሊል ስርአት የሚፈፀምላቸው ወጣቶች ራሳቸውን ከዝሙት ጠብቀው በድንግልና የፀኑ መሆን አለባቸው።
3.መፈቃቀድ
የሚጋቡት ወጣቶች አንዳቸው ሌላውን ሊፈቅዱ ሊወዱ ያስፈልጋል። የሁለቱ መፈቃቀድ ሳይኖር በወላጆች ተፅእኖ ብቻ ስርአተ ተክሊል ጋብቻ ሊፈፀም አይችልም። ለዚነው በስርአቱ ላይ አንደኛው ሌላውን «ወድጀ ፈቅጀ የምቀርበው»አንዳንድ ግዜ ለምንድነው ወደ ቤተ- ክርስቲያን ተቀብያታለው ወይም ተቀብየዋለው ብለው ቃል የሚገቡት።
4.እድሜ
የሚጋቡት ወጣቶች እድሚያቸው ትዳር የሚጠብቀውን ሀላፊነት ለመወጣት ብቁ ሊሆኑ ያስፈልጋል ለዚህም አስቀድሞ በፍትሀ ነገስት እንደተገለፀው ሴቷ 15 ወንዱ ደግሞ 18 አመት የሞላቸው መሆን አለባቸው። እንደዚህም ሁኖ ሌሎች ነገሮች ካልተሟሉ ከዚህ በላይ
ቢሆን መልካም ነው።
5.የንስሀ አባት ምስክርነት
ስርአተ ተክሊል የሚፈፀምላቸው ወጣቶች አስቀድመው ንስሀ እየገቡ ንፅህናቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ የግድ የንስሀ አባት ሊይዝ ያስፈልጋል። ለንስሀ አባታቸውም ስለጋብቻቸውም ሆነ ስለ ማንኛውም ህይወታቸው ሊያማክሩ ይገባል ። በዘመናችን አልፎ አልፎ እንደሚታየው «ገንዘብ ከፍየ ወይንም ደብረ ሊባኖስ ሂጀ አገባለው» እያሉ ተደብቆ ስርአተ ተክሊል መፈፀም አይቻልም። ተጋቢወች ካላይ የተጠቀሱትን ማሟላታቸውን በንስሀ አባት ሊረጋገጥና ይህም ሊመሰከርላቸው ያስፈልጋል። በመሆኑም የተጋቢወች መንፈሳዊም ሆነ ስጋዊ ኑሮ በንስሀ አባታቸው ፊት የተገለጠ ሊሆን ይገባል።
6.ሁለቱም ተጋቢወች ወይንም ከሁለቱ አንዱ ወገን ራሱን የቻለ ሊሆን ያስፈልጋል።
የኢኮኖሚ አቅማቸውም ቤተሰቡን ለማስተዳደር በቂ መሆኑ ሊረጋገጥ ይገባል።
የኢኮኖሚ አቅማቸውም ቤተሰቡን ለማስተዳደር በቂ መሆኑ ሊረጋገጥ ይገባል።
7.ስለ ትዳር ማወቅ (በቂ ግንዛቤ)
ተጋቢወች ከመጋባታቸው በፊት ስለ ትዳርና አጠቃላይ ስለ ተክሊል ጋብቻ በሚገባ ሊያውቁ ይገባል። ትዳር በሶስተኛው ሰው ግፊት የሚፈፅምና ለጥቅማጥቅም ተብሎ ካልሆነም ለሙከራ የሚገባበት ሳይሆን ከልብ በመነጨ ፍቅርና ለትዳር ባለወ ግንዛቤ ስለትዳር በቂ
እውቀት መኖር ግድ ይላል ስለተክሊም ቢሆን ከ አባቶችና በሰንበት ትምህር ቤት በቂ እውቀት ሊኖር ይገባል እንግዲህ ተጋቢወች ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች ካሟሉ የተቀደሰውን የስርአተ ተክሊል ጋብቻ ሊፈፀምላቸው ይችላል። በተረፈ ከአፅዋማት ቀን በቀር ይፈፀማል።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!