Our Church – ስለ ቤተክርስትያናችን

Download PDF
  • new
  • web2sela
  • cross_Edited
  • SAM_1146_Edited
  • image012saints
  • SAM_1155
  • 01crusification
  • SAM_1170
  • mary
  • SAM_1156
  • image010
  • SAM_1165DDD
  • Tekle
  • eotcc5
  • webnn
  • SAM_1172
  • SAM_1096_Edited
  • SAM_1147
  • Trin
  • SAM_117 new
  • Copy of SAM_1165
  • B5E243E0-6612-40E5-B99C-3DCA5029E225_w640_r1_s
  • SAM_1146
  • webtekl
  • cross
  • SAM_1173
  • double2
  • lalibela-During%20Celabration
  • SAM_1167MM
Ajax Slider by WOWSlider.com v5.2

 

የቅዱስ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በኦታዋ ከተቋቋመበት ቀን ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ ለአመታት የራሱ የሆነ ቤተክርስትያን ሳይኖረው ቆይቶ ‹‹ወደ ተራራ ውጡ እንጨትም አምጡ ቤቱንም ስሩ እኔም በሱ ደስ ይለኛል  እኔም እመሰገነናለሁ ይላል እግዚአብሔር ›› ትንቢተ ሃጌ ም. 1 ቁጥር 8 የሚለውን ቅዱስ ቃል ሁል ጊዜ በማሰብ ይሄው ዛሬ ቁጥራቸው ጥቂት በሆነ የቤተክርስትያን አባላት ያላሰለሰ ጥረትና ትብብር በእግዚአብሔር ቸርነትና ድንቅ ስራ ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ የራሳችን ህንፃ ቤተክርስትያን ባለቤት ሆነናል፡፡ ለዚሁም እግዚአብሔር ስሙ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን አሜን !!!!!!

ቤተክርስትያናችን በኦታዋና አካባቢው ለሚገኙ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የቅዳሴ ፡ የክርስትና ፡ የፍታትና ፡ የሰርግ አገልግሎት በመስጠት ኦርቶዶክስ ወገኖቻችንን በማገልገል ላይ ትገኛለች፡፡

የወደፊት የቤተ ክርስትያን ተረካቢ የሆኑትን ህፃናት ኢትዮጵያዊነታቸውን ፡ ኦርቶዶክስ ሃይማኖታቸውን፡ ስርዓታቸውን ቋንቋቸውንና፡ ባህላቸውን፤ ከወላጆቻቸው ቀጥሎ ማሳወቅና ማስተማር የቤተ ክርስትያን ሃፊነት ነው፡፡ ይህን አደራ እንደውም የአደራ አደራ የምትወጣበትን በማመቻቸት ከወላጆች ጋር በመምከርና በመተባበር እቅዱን በመተግበር ረገድ      በቤተ ክርስትያናችን የምድር ቤት አዳራሽ የሚገኙትን ክፍሎች ለማስተማረያ በመጠቀም ጥረት እያደረገች ነው፡፡

ቤተክርስቲያናችን ይህን አደራዋን በተደራጀና ሰፋ ባለ መልኩ በብቃት እንድትወጣ ይረዳ ዘንድ እንዲሁም በቤተ ክርስቲያናችን የምትሰጠውን ግልጋሎት ለማጠንከርና ለማዳበር ፡ እያደገ የመጣውን የአባላት ቁጥር በተገቢው መንገድ መዝግቦ ለመያዝ እንዲሁም የቤተክርስትያኑን የንብረት አያያዝ የተቀላጠፈ ለማድረግ ይረዳ ዘንድ የኮምፕዩተር መዝገብ አያያዝ በስራ ላይ አውሏል፡፡ በተጨማሪም ስለ ቤተ ክርስቲያናችን እንቅስቃሴ አጠቃላይ ግንዛቤ እንዲኖርና የአገልግሎት አሰጠጣጥን ለመሰፋፋት ይረዳ ዘንድ ቤተ ክርስቲያናችን የድህረ-ገፅ ዘርግቷል፡፡ በዚህ የተቀደሰ ምግባርና ቤተ ክርስትያኑ ከተቋቋመበት ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ጊዚያቸው እውቀታቸውን ገንዘባቸውን መስዋዕት በማድረግ አብረሮ በመጓዝ የቤተ ክርስትያኗ ማገርና ምሶሶ በመሆን ቤተ ክርስቲያኗ ዘሬ
ለደረሰችበት የእድገት ደረጃ ያበቃት ያላሰለሰ አስተዋዕፆ በማድረግ ላይ ባሉት የቅዱስ ተክለሃይማኖት በቤተ ክርስቲያን ካህናት ፡ ዲያቆናት ፡ መዘምራን ፡ የሰበካ ጉባዔ አስተዳደር ፡ እንዲሁም ውድ ምዕመናንና የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች ነው፡፡

የአባላትና ምዕመናን ንቁ ተሳትፎ በቤተክርስትያናችን ውስጥ ለመሚሰጠው መንፈሳዊና ማህበራዊ አገልግሎት ላይ አይነተኛ እንደምታ ስለሚነኖረው በተለየያየ የስራ ዘርፍ በጉልበት በገንዘብና በአውቀት አስተዋእፆ ለማድረግ የምትፈልጉ ውድ የቤተክርስቲያን ወዳጆች ሁሉ ቤተክርስቲያናችን ከዚህ በፊት እንደሚያደርገው አሁንም ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ወስብሀት ለእግዚአብሔር !!!!

Adminstration – አስተዳደር

Contact Us – አድራሻችን

Services – አገልግሎቶች

History – የቤተክርስትያናችን ታሪክ

History of St. Tekle Haimanot – የቅዱስ ተክለሃይማኖትታሪክ