በዚህ ገፅ ስለ ያገኛሉ

የቅዱስ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በኦታዋ ከተቋቋመበት ቀን ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ ለአመታት የራሱ የሆነ ቤተክርስትያን ሳይኖረው ቆይቶ ‹‹ወደ ተራራ ውጡ እንጨትም አምጡ ቤቱንም ስሩ እኔም በሱ ደስ ይለኛል  እኔም እመሰገነናለሁ ይላል እግዚአብሔር ›› ትንቢተ ሃጌ ም. 1 ቁጥር 8 የሚለውን ቅዱስ ቃል ሁል ጊዜ በማሰብ ይሄው ዛሬ ቁጥራቸው ጥቂት በሆነ የቤተክርስትያን አባላት ያላሰለሰ ጥረትና ትብብር በእግዚአብሔር ቸርነትና ድንቅ ስራ ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ የራሳችን ህንፃ ቤተክርስትያን ባለቤት ሆነናል፡፡ ለዚሁም እግዚአብሔር ስሙ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን አሜን !!!!!!

ቤተክርስትያናችን በኦታዋና አካባቢው ለሚገኙ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የቅዳሴ ፡ የክርስትና ፡ የፍታትና ፡ የሰርግ አገልግሎት በመስጠት ኦርቶዶክስ ወገኖቻችንን በማገልገል ላይ ትገኛለች፡፡

የወደፊት የቤተ ክርስትያን ተረካቢ የሆኑትን ህፃናት ኢትዮጵያዊነታቸውን ፡ ኦርቶዶክስ ሃይማኖታቸውን፡ ስርዓታቸውን ቋንቋቸውንና፡ ባህላቸውን፤ ከወላጆቻቸው ቀጥሎ ማሳወቅና ማስተማር የቤተ ክርስትያን ሃፊነት ነው፡፡ ይህን አደራ እንደውም የአደራ አደራ የምትወጣበትን በማመቻቸት ከወላጆች ጋር በመምከርና በመተባበር እቅዱን በመተግበር ረገድ      በቤተ ክርስትያናችን የምድር ቤት አዳራሽ የሚገኙትን ክፍሎች ለማስተማረያ በመጠቀም ጥረት እያደረገች ነው፡፡

ቤተክርስቲያናችን ይህን አደራዋን በተደራጀና ሰፋ ባለ መልኩ በብቃት እንድትወጣ ይረዳ ዘንድ እንዲሁም በቤተ ክርስቲያናችን የምትሰጠውን ግልጋሎት ለማጠንከርና ለማዳበር ፡ እያደገ የመጣውን የአባላት ቁጥር በተገቢው መንገድ መዝግቦ ለመያዝ እንዲሁም የቤተክርስትያኑን የንብረት አያያዝ የተቀላጠፈ ለማድረግ ይረዳ ዘንድ የኮምፕዩተር መዝገብ አያያዝ በስራ ላይ አውሏል፡፡ በተጨማሪም ስለ ቤተ ክርስቲያናችን እንቅስቃሴ አጠቃላይ ግንዛቤ እንዲኖርና የአገልግሎት አሰጠጣጥን ለመሰፋፋት ይረዳ ዘንድ ቤተ ክርስቲያናችን የድህረ-ገፅ ዘርግቷል፡፡ በዚህ የተቀደሰ ምግባርና ቤተ ክርስትያኑ ከተቋቋመበት ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ጊዚያቸው እውቀታቸውን ገንዘባቸውን መስዋዕት በማድረግ አብረሮ በመጓዝ የቤተ ክርስትያኗ ማገርና ምሶሶ በመሆን ቤተ ክርስቲያኗ ዘሬ
ለደረሰችበት የእድገት ደረጃ ያበቃት ያላሰለሰ አስተዋዕፆ በማድረግ ላይ ባሉት የቅዱስ ተክለሃይማኖት በቤተ ክርስቲያን ካህናት ፡ ዲያቆናት ፡ መዘምራን ፡ የሰበካ ጉባዔ አስተዳደር ፡ እንዲሁም ውድ ምዕመናንና የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች ነው፡፡

የአባላትና ምዕመናን ንቁ ተሳትፎ በቤተክርስትያናችን ውስጥ ለመሚሰጠው መንፈሳዊና ማህበራዊ አገልግሎት ላይ አይነተኛ እንደምታ ስለሚነኖረው በተለየያየ የስራ ዘርፍ በጉልበት በገንዘብና በአውቀት አስተዋእፆ ለማድረግ የምትፈልጉ ውድ የቤተክርስቲያን ወዳጆች ሁሉ ቤተክርስቲያናችን ከዚህ በፊት እንደሚያደርገው አሁንም ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ወስብሀት ለእግዚአብሔር !!!!

በኦታዋ የቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስትያን አመሰራረትና እድገት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አሃዱ አምላክ አሜን!

ከሁሉ በፊት ተበታትነን እንዳንቀር ስለአሰባሰበን ሳንፈልገው ለፈለገን በደለኞች ሁነን ሳለ በደላችንን ላልቆጠረብን በአንደ ላይ ሁነን ስሙን እንድናመሰግን ስልፈቀደልን አነሳስቶ ለአስጀመረንና ለኣአስፈፀመን ለፍቅር አምላክ ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይድረሰው አሜን

ቤተ ክርስትያኑ እንዴት ተመሰረተ ? ለምስረታው ምክንያት የሆነው ምንድነው ? አላማውስ ምን ነበረ?

ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ  የቤተ ክርስትያናችንአመሰራረትና እድገትን

የአቡነ ተክለሃይማኖት ገድል ባጭሩ

ዝክረ ጻድቅ ይሄሉ ፣ የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም  ይኖራል  መዝሙር ፻፲፩፥፮

(ከማህደረ ቅዱሳን ግንቦት ፲፱፻፺፮ ዓ.ም. እትም የተወሰደ)

Church Administrator
ዋና አስተዳዳሪ

Melake Genet Memher Senay Admassu

መላከ ገነት መምህር ሰናይ አድማሱ

Church Administrator
ዋና አስተዳዳሪ

Samson Ambaye

ሳምሶን አምባዬ

Deacon
ዲያቆን

Melaku Habtehana

መላኩ ሀብተሀና

Deacon
ዲያቆን

Yosef Hailu

ዮሴፍ ኃይሉ

Deacon
ዲያቆን

Besufekad Habtehana

በሱፈቃድ ሀብተሀና

Deacon
ዲያቆን

Tadesse Gesesse

ታደሰ ገሠሠ

Deacon
ዲያቆን

Board of directors
ሰበካ ጉባኤ

Ato Debebe Emissa

አቶ ደበበ ኢሚሳ

Chairperson

Ato Shiferaw Adal

አቶ ሽፈራው አዳል

Vice Chair

Ato Kefyalew Gemeda

አቶ ከፍያለው ገመዳ

Financial Officer

W/o Gulilat Dinsa

ወ/ሮ ጉልላት ድንሳ

Cashier

Ato Bruck Wubete

አቶ ብሩክ ዉበቴ

Secretary

Artist Abebe Addis

አርቲስት አበበ አዲስ

Member

W/o Hanna Gebre

ወ/ሮ ሃና ገብሬ

Member

Ato Adebabay Kinde

አቶ አደባባይ ክንዴ

Member

W/o Meskerem Feyissa

ው/ሮ መስከረም ፈይሳ

Member

Ato Solomon Zeleke

አቶ ሰለሞን ዘለቀ

Member

D/n Akalewold H/selassie

ዲ/ን አካለወልድ ሃ/ስላሴ

Member