
ስም አንድ ሰው ከሌላው ተለይቶ የሚታወቅበት ነው። ሰው ከእናትና ከአባቱ ሲወለድ ስም እንደሚወጣለት ሁሉ በጥምቀት ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ሲወለድም ስም ይወጣለታል፡፡ ስለዚህ አንድ ክርስቲያን ሁለት ዓይነት ስሞች ሊኖሩት ይችላል። አባትና እናት የሚያወጡለት ስም የተጸውኦ ስም ይባላል፡፡ በጥምቀት ጊዜ የሚወጣለት ስም ደግሞ የክርስትና ስም ይባላል፡፡ በጥምቀት ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና ይገኝበታል፡፡ በክርስቶስ የሚያምን ሰው ክርስቲያን ሲባል እምነቱ ደግሞ ክርስትና ይባላል። ክርስቲያን ማለት የክርስቶስ ወገን የሆነ ማለት ነው። በመሆኑም በክርስቶስ አምነን በሥላሴ ስም መጠመቃችንን የሚገልጸው ስም ስመ ክርስትና ይባላል። ስያሜውም ተጠማቂው ከተጠመቀበት ዕለት ጋር ተያይዞ ሊሰየም ይችላል። በመንፈሳዊ አገልግሎት ስንሳተፍ ስመ ክርስትናችንን እንጠቀማለን፡፡ የክርስትና ስም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትውፊት ያለው ነው፡፡ ይህም እግዚአብሔር አብራምን አብርሃም፣ ያዕቆብን እስራኤል፣ ሰምዖንን ጴጥሮስ፣ ሳውልን ጳውሎስ እንዲባል እንዳደረገው ያለ ነው፡፡
$80 / Once / Per Accommodation