አባ ኪሮስ

Download PDF

አባ ኪሮስ አባቱ ንጉስ ዮናስ እናቱ አንስራ ይባላሉ፡፡ ሀገሩ ሮም ነው፡፡ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ነበሩና አቡነ ኪሮስ በታህሳስ 8 ወለዱ፡፡ አቡነ ኪሮስ የመጀመሪያ ስሙ ዲላሶር ይባል ነበር፡፡ በኋላ አባቱ ከሞተ በኋላ ሀብቱን ከወንድሙ ተካፍሎ ለድሆች መጽውቶ ዓለምን ንቆ መንኖ ሄደ፡፡ ከአባ በቡነዳ ገዳም ገባ፡፡ በ17 ዓመቱ ሥርዓተ ምነኩስናን ተማረ፡፡ በአባ በቡነዳ እጅ መነኮሰ፡፡ ከዚህ በኋላ በጾም በጸሎት ተወስኖ ኖረ፡፡ስለ ዓለም መከራ ለ40 ዘመን ተኝተው ሲጸልዩ እላያቸው ላይ ሳር በቅሎባቸው ሳለ መላእክት መጥተው ተነስ ቢሉት አዳም የፍጡር ቃል ሰምቶ ወድቀዋል ጌታዬ ድምጹን ያሰማኝ አላቸው በኋላ ኪሩቤል አንስቶ ወስዶ ገነት አሳይተውት ጌታችንም ቃል ኪዳን ሰቷቸዋል።

ቃል ኪዳናቸውም ፡- መካኖች ልጀ የሌላቸው ገድሉን አቅፈው ቢያለቅሱ ጸበሉን ቢጠጡ ስምህን ቢጠሩ፤ የመካኒቱን ማህጸን እከፍታለሁ፡፡ የሚሞትባቸውን እንዳይሞተባቸው አደርጋለሁ፡ በንጹ ገንዘቡ ቂምና በቀል ሳይዝ በህግ በስጋውና በደሙ የጸና ሰው በስምህም በተሠራው ቤተክርስቲያን ጧፍ ዘይት ያበራ መገበሪያ ያመጣውን ልጅ አሰጠዋለሁ፡፡ ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ከዚም በኋላ በተወለዱ 270 ዓመታቸው በዛሬዋ ዕለት ሐምሌ 8 አርፈዋል።

aba kiros

ከቅዱሳን ሁሉ ረድኤታቸውንና በረከታቸውን አሳድርብን፡፡ በድፍረት፣ በትዕቢት በመናቅም በቅዱሳን ላይ የሚናገሩ የሽንገላ አንደበት ዲዳ ይሁኑ መዝሙር 30፡18 አንዳንዶችን በቅዱሳን ላይ ተነስቷልና ይቅር ይበላቸው፤ ልቦና ይስጣቸው መድሃኒትዓለም የሚያደርጉትን አያቁምና ይቅር በላቸው ያለው ጌታ ይቅር ይበላቸው፡፡ …እንግዲህ እግዚአብሔር የመረጠውን ማን ይከሳል። ሮሜ 8፡28-31 “የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል እናንተን የጣለ እኔን ይጥላል እኔን የጣለ የላከኝን ይጥላል።” ሉቃ. 10፡16

“ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ መዝሙር” 111፡6

+++…ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል… እውነት እላችዃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም…+++። ማቴ.10፡40-42

ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብዕ።