History of St. Tekle Haimanot – የቅዱስ ተክለሃይማኖትታሪክ

Download PDF

“ዝክረ ጻድቅ ይሄሉ ፣ የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም  ይኖራል”    መዝሙር ፻፲፩፥፮

የአቡነ ተክለሃይማኖት ገድል ባጭሩ

(ከማህደረ ቅዱሳን ግንቦት ፲፱፻፺፮ ዓ.ም. እትም የተወሰደ)

Abune Tekel Haimanot

መታሰብያቸው ለዘላለም ከሚኖረው ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖተ ናቸው፡፡

ቅዱስ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ቅዱስ ጸጋ ዘኣብና ቅድስት እግዚእሐርያ ከሚባሉ ቅዱሳን በሰሜን ሸዋ ሃገር ሰብከት በቡልጋ አውራጃ    ደብረጽላልሽ በተባለው ስፍራ መጋቢት ፳፬ ቀን በብሥራት መልአክ ተፀንሰው በ፲፩፻፺፯ ዓም ታህሳስ ፳፬ ቀን ተወለዱ። ጻድቁ ቅዱስ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት  በእናታቸው ማህፀን ሳሉ ልዑል እግዚአብሔር ስለመረጣቸው በተወለዱ በሶስት ቀናቸው በእናታቸው በቅድስት እግዚእሐርያ እቅፍ ሆነው አሃዱ አብ ቅዱስ አሃዱ ወልድ ቅዱስ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብለው ለሥላሴ እንደ አባታቸው ቅዱስ ጸጋ ዘኣብ ምስጋና አቅርበዋል።

አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት በቀድሞ አጠራር ዞረሬ የአሁኑ የታኢሳ ሚካኤል ክርስትና ሲንሱ የክርስትና ስማቸው ፍስሐፅዮን ተባለ። እንደ ህፃን በጥቂቱ ሲያድጉ ከቆዩ በኋላ በሰባት ዓመታቸው ከቅዱስ ጸጋ ዘኣብ ትምህርት ጀምረው በስምንት ዓመታት ውስጥ ብሉይ ከሐዲስ ትርጓሜና ሥርአት ቤተ ክርስትያን አጠናቀቁ።  አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት በተወለዱ በ፲፯ ዓመታቸው በዘመኑ ከነበሩት ግብፃዊ ጳጳስ ኣባጌርሎስ ድቁና ማእረግ ተቀብለው ሲመለሱ የተለያዩ ተአምራት በጉዞአቸው ላይ አሳይተዋል። በተወለዱበት ደብር በድቁና ማዕረግ እያገለገሉ በቁመት በጥበብ እየጎለመሱ ሲሄዱ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት በተወለዱ በ ፳፬ ዓመታችው ቅዱስ ጸጋ ዘኣብና እናታችው ቅድስት እግዚእሐርያ በተከታታይ ወራቶች ውስጥ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩዋቸው።

“ሰው አለምን ቢገዛ ነፍሱን ግን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል ። ነፍሱን ሊያድናት የወደደ መስቀሌን ተሸክሞ ይከተለኝ” የሚለውን

አምላካዊ ቃል አስበው ከጓደኞቻቸው ጋር አራዊት ሲያድኑ ከዛሬ ጀምሮ አራዊት ሳይሆን ሰዎች ታድናለህ ተብለው በታዘዙት መሰረት ከኣባት ከእናታቸው ያገኙትን ሃብት ንብረት በሙሉ ለነዳያንና ለቤተክርትያን መፅውተው እንደ ሐዋርያ ለማስተማር ፥ እንደ ሰማዕታት መከራ ለመቀበል ፥ እንደ መኖክሳት በሕርመት በጾም በጸሎት በብሕትውና ለመኖር ፥ ቤታቸውን ክፍት ትተው የዳዊትን መዝሙር
እየዘመሩ ሄዱ።

ከዚያ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዲስ ሐዋርያ ዘኢትዮጵያ ብሎ ሲሾማቸው ስማቸውም ፍስሐፅዮን መባላቸው ቀርቶ ተክለ አብ
ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ወይም ተክለ ሃይማኖት ተብለው እንዲጠሩ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል አዘዛቸው።

ብፁወ ቅዱስ ፃድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት የዘመድ ናፍቆትና የገንዘብ ፍቅር ጨርሶ ጠፋለትና  የሚያስበውና የሚሰራው የእግዚአብሔርን ሕግ ብቻ ሆነ። ያለአንተ ጠባቅዬ ብወድቅ የሚናሳኝ ብጠቃ የሚረዳኝ የለም እያለ ከእግዚአብሔር ጋር በመነጋገር ማስተማርና ድውያንን መፈወስ ጀመረ። ቤቱም ከፍቶ ጌታዬ ቤቴን ከፍቼ ትቼ ስለሄድኩኝ አንተም የመንግስት ሰማያትን በር ክፈትልኝ
ብሎ የሐዋርያትን ሥራ ወንጌልን ለማስተማር ቤቱን ጥሎት ሄዿል። ትምህርቱና ተአምራቱ ሁ ሉ በየሀገሩ ደርሶ በእርሱ ስብከት ያመኑት ሰዎች ለእንጨት ለድንጋይ ከዚህም ሌላ ልዩ ልዩ ለሆኑ ጣኦታት የሚሰው አሉ ብለው ነገሩት።  በነሱ መሪነት ሄዶ እንደነገሩት ሆኖ አገኘው። ምን ምን ታመልካላችሁ ቢላችው የምንሰግድለት የምናመልከው ዛፍ አለ አሉት ። ስትሰግዱለት ምን ይላቹሃል ? አላቸው።
ከዛፍ ላይ ሆኖ ፈጣርያችሁ እኔ ነኝ ይለናል አሉ። እኔም እንድሰግድለት ይዛችሁኝ ሂዱ ኣላቸው ። ይዘውት ሲሄዱ ምን ይዛችሁብኝ መጣችሁ ብሎ ጮኸባቸው። ፈጣሪያችን የጠላህ ኃጢአተኛ ብትሆን ነው እሱ ኃጢአተኛውን ከሩቅ ያውቃልና ተመለስ አይሆንም
አሉት። ከዚያ ተመልሶ በፈጠርከው ፍጥረት ሰይጣን ለምን ይጫወትበታል? በሎ ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክትና አንቺ እንጨት
ሰይጣን የሚያስትብሽ ዛፍ ተነቅለሽ ነዶ በሎ ጠራት። እርሷም ከነስሯ ተነቅላ ወደ እርሱ እየሮጠች መጣች ። ወደ እርሱም ስትመጣ
ከስሯ ያለውን አፈርና ጠጠር እያወናጨፈጭ ፳፬ ሰዎች ፈጀች።ያ እንጨቷ ለይ የነበርው ሰይጣን ወደየት ልሂድ? ብሎ ጮኸ ። በል ቀድሞ እንዳሳትካቸው በቃልህ አምላክ አለመሆንህን ግለጽና ውጣ ብሎ አዘዘው ። እርሱም ለቃሉ ታዞ ተናግሮ ወጥቶ ሄደ ። እነዚያን አሳምኖ በስመ አብ ወወልድ ወ መነፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ብሎ አጠመቃቸው ። እንጨቷም የፈጀቻቸውን ሰዎችም አስነስቷል ።
ከዚህ በኋላ ቤተ ክርስትያን አሳንጾ የሚያስተምር ካህን መድቦላቸው እግዚአብሔር ወደ ጠራው ቦታ ሄዷል።

ቅዱስ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያስተምሩ የጠራቸው በይፋት በአማራ ሳዶትና
በሸዋ ክፍለ ሀገር ስለ ነበር ይህን ትእዛዝ ከፈፀመ በኋላ የተጠራው ወደ ጉራጌ ነበር። እዚያም አስተምሮ አጥምቆ የአምላክን ፍቃድ እንደፈፀመ ለታላቅ ተጋድሎና አገልግሎት ወደ ወላሞ ሄደ ። ከወላሞ አገር የነገሰው ሞተሎሚ የሚባለው ንጉስ ነበረ ። ሞተሎሚ
የሚያመልከው በእግዚአብሔር ሳይሆን በጣኦት ነበር ። ፃድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ከዚያ እንደደረሰ ሞተሎሚ የሚያመልካቸውን ጣኦታት ስለሰበረ ንጉሱ ሳይሰማ አይገደልም ብለው አስረው ቀፈረ ውድም ለሚባለው ለንጉሱ ሹም አስረክበውታል። ሙሉ ገድላቸውን እዚህ ላይ ይመልከቱ…..